Central Ethiopia Regions IPDC

Business

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኢንዱስትሪ ምርቶችን መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል (Recycling) በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ የውይይት ተካሄደ:: (ቀን፡ ሚያዝያ 08 ቀን 2018 ዓ.ም:


News Image
News Image
News Image
News Image
News Image
News Image
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በክልሉ የሚገኙ ከተሞችን የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግና የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማሳደግ በአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኢንዱስትሪ ምርቶችን መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል (Recycling) በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ የውይይት ተካሄደ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በክልሉ የሚገኙ ከተሞችን የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግና የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማሳደግ በአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል። በዚህም መሠረት በሆሳዕና እና በወልቂጤ ከተሞች የኢንዱስትሪ ምርቶችን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል (Resource Recycling ) ዘርፍ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞችን አቅም ለመገንባት የሚያስችል ከፍተኛ የሥራ አመራር ውይይት በዛሬው ዕለት በዋናው መሥሪያ ቤት ተካሂዷል። የውይይቱ ዋና ዋና ነጥቦች እንደሚከተለው ቀርበዋል፦ 1. የአማካሪ ድርጅቱ ጥናትና ግኝቶች "ስማርት ካሪየር ሶሉሽንስ" (Smart Career Solutions) የተሰኘው አማካሪ ድርጅት በሆሳዕና እና ወልቂጤ ከተሞች በሚገኙ ኢንተርፕራይዞች ላይ ያደረገውን የክፍተት ዳሰሳ ጥናት ሪፖርት አቅርቧል። ሪፖርቱ በዋናነት ኢንተርፕራይዞቹ በምርት ሂደት ውስጥ ተረፈ-ምርቶችን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል ረገድ ያሉባቸውን የዕውቀት፣ የቴክኖሎጂ እና የሥርዓት ክፍተቶች በዝርዝር አመልክቷል። በተጨማሪም በጥናቱ የተለዩትን ክፍተቶች መሠረት በማድረግ፣ ምርትን መልሶ ጥቅም ላይ የሚያውሉ (Recycling Enterprises) ኢንተርፕራይዞችን በቴክኖሎጂ ለማገዝ ስምምነት ላይ ተደርሷል። በዚህም መሠረት፦ ለኢንተርፕራይዞቹ የሚሰጡ የማሽነሪ ድጋፎችን ዓይነትና ጥራት የሚወስን ዝርዝር የዕቃ መግለጫ (Technical Specification) እንዲዘጋጅ አቅጣጫ ተቀምጧል። ድጋፉ ኢንተርፕራይዞቹ ጥሬ ዕቃን በቁጠባ እንዲጠቀሙና የአካባቢ ብክለትን እንዲቀንሱ ታስቦ የሚከናወን መሆኑ ተገልጿል። በመጨረሻም ኢንተርፕራይዞቹ የሚሰጣቸውን ማሽነሪዎች በአግባቡ እንዲያንቀሳቅሱና የምርት ጥራታቸውን እንዲያሳድጉ ተከታታይ የሙያና የቴክኒክ ሥልጠና ከነገ ጀምሮ በሚሰጥበት ሁኔታ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል። ሥልጠናው በንድፈ-ሐሳብ ብቻ ሳይወሰን በተግባር የተደገፈ እንዲሆንና ውጤታማነቱም በኮርፖሬሽኑ በኩል ክትትል እንደሚደረግበት ታውቋል። በውይይቱ ወቅት የኮርፖሬሽኑ ማኔጅመንት አካላት በሰጡት መመሪያ መሠረት፣ ይህ የድጋፍ መርሃ-ግብር የሆሳዕና እና የወልቂጤ ከተሞችን የኢንዱስትሪ እንቅስቃሴ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግርና የክብ ኢኮኖሚ (Circular Economy) ሥርዓትን በክልሉ ለማስፈን ትልቅ ሚና የሚጫወት ነው ሲሉ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል። ለተጨማሪ መረጃ፡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የማርኬቲንግ እና ቢዝነስ ዲቨሎፕመንት ዳይሬክቶሬት


Post Viewer :0 Post By : Central Ethiopia IPDC Post Date : 2026-04-16 Download File